ኢትዮጵያ የታገሰችው የሱዳንን ህዝብ ስለምታከብር እንጂ ፈርታ አይደለም!
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ሱዳን ቤንሻንጉልን የራሷ ለማድረግ የምታደርገው እንቅስቃሴ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና እያለ በዚህ መንገድ ለመፈፀም የምትሞክረው ህገወጥ ድርጊት በኢትዮጺያ በኩል ፍፅም ተቀባይነት እንደሌለው ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የገለፁት፡፡
ሱዳን የኢትዮያን መሬት የመያዟና ኢትዮጵያዊያን አርሶአደረች ማፈናቀሏ ሳያንሳት ቤንሻንጉልን የራስዋ ለማድረግ መሞከሯ የለየለት ህገወጥነት ነው ብለዋል።
ሱዳን የህዳሴ ግድቡን ድርድር የተጣረሱ መረጃዎች በማውጣትና ከኢትዮጵያ ጋር በማስተሳሰር ሂደቱን ለማደናቀፍ ከምታደረገው ተግባር እንድትቆጠብ ኢትዮጵያ አስጠንቅቃለች።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የአለም አቀፍ ህግጋትን ስታከብር እንኖረችና አሁንም እያከበረች እንደሆነ ዓለም የሚያውቀው በመሆኑ ይህን እውነታ ለማስቀየስ የሚደረገው ጥረት ከንቱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በመግለጫ የጀመረችው ማስጠንቀቅያ በቀጠይ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት ቃል አቀባዩ እስካሁን ያሳየችው ትዕግስት የሱዳንን ታላቅ ህዝብ ስለምታከብር እንጂ አቅም ስላነሳት እንዳልሆነ ገልፀዋል።