loading
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚወዳደሩበትን የምርጫ ወረዳ ፓርቲዉ አሳታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚወዳደሩበትን የምርጫ ወረዳ ፓርቲዉ አሳታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ላማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በተከታታይ በፌስቡክ ገጹ እጩዎቹን እያሰተዋወቀ ሲሆን ፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ወረዳ 23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ መሆናቸዉን አስታዉቋል፡፡

የምርጫ ወረዳ 23 የሚያጠቃልላቸው አካባቢዎች ከሳርቤት ቄራ ድልድይ ወንዙን ይዞ ከአፈሪካ ህብርት በታች፤ ሳርቤት መካኒሳ ድልድይ፤ ሳርቤት ካርል አደባባይን ይዞ ኦልድ ኤርፖርት እስከ ቶታል 3 ቁጥር ማዞርያ፤ ቆሬ ድልድይ ወንዙን ይዞ መካኒሳ ድልድይ ፤ አቦ ማዞሪይ ቫቲካን ኢምባሲ ፤ ከመካኒሳ ታክሲ ተራ ጀርመን አደባባይ ኃይሌ ጋርመንት፣ ለቡ ከፉሪ ኦሮሚያ ክልል ወስን፣ ጀሞ 1 ፣ 2 እና 3 ኮንዶሚንየም፣ መካኒሳ ሚካኤል፣ ቆሬ፣ ቆሼ፣ ጀሞ
መሰታወት ፋብሪካ ወደ ዘነበ ወርቅ፣ ቶታልና አየር ጤና አካባቢዎች መሆናቸዉን ፓርቲዉ አስዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *