loading
የአሜሪካ ጦር የሞዛምቢክ ባህር ሃይል የጂሃዲስቶችን አመጽ ለመውጋት ያግዘው ዘንድ ሊያሰለጥን መሆኑ ተነገረ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 የአሜሪካ ጦር የሞዛምቢክ ባህር ሃይል የጂሃዲስቶችን አመጽ ለመውጋት ያግዘው ዘንድ ሊያሰለጥን መሆኑ ተነገረ ፡፡ የሞዛምቢክ ባህር ሃይል በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ካቦ ዴልጋዶ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የጂሃዲስት አመጽ ለመዋጋት የሚያስችለውን አቅም የአሜሪካ ልዩ ኦፕሬሽን ሃይል ለሁለት ወራት እንደሚያስታጥቀው በማፑቶ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በአካባቢው አል- ሸባብ በመባል የሚታወቁት የታጠቁት ቡድኖች፤ ከታንዛኒያ ጋር በሚዋሰነውና በተፈጥሮ ጋዝ የበለፀገ አካባቢ በሆነችው ስትራቴጂካያዊ ካቦ ዴልጋዶ ውስጥ ከሶስት ዓመታት በላይ የሽብር ተግባራትን እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ በ2019 ዓ.ም ራሱን እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አድርጎ ለሚቆጥረው አይ.ኤስ ታማኝ ለመሆን ቃል መግባታቸውም ተነግሯል ፡፡

ኤምባሲው ከስልጠናው በተጨማሪ የህክምና እና የግንኙነት መሳሪያዎችን አበርክቷል የተባለ ሲሆን የጋራ የተቀናጀ የልውውጥ ስልጠና በተባለው ፕሮግራም ላይ የሚሳተፍ የአሜሪካ ጦር ሃይል አስቀድሞ በሞዛምቢክ ተገኝቷል ተብሏል ፡፡ ይህ እርምጃ የተወሰደው አሜሪካ በሞዛምቢክ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ውስጥ አማፂ ቡድኖችን እንደ የውጭ አሸባሪ ድርጅቶች መመደቧን ተከትሎ መሆኑን የአፍሪካ ኒውስ እና ኤ.ኤፍ.ፒ መረጃ ያመላክታል፡፡

በፈረንሣይ የነዳጅ እና ጋዝ ኩባንያ ቶታል ከሚሠራው በበርካታ ቢሊዮን ዩሮ ጋዝ ፕሮጀክት በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ብቻ ርቀት ላይ በሚገኜው አካባቢ በታህሳስ ወር መጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄዱ ጥቃቶች ጉዳዮ ከፍ ባለ እይታ ውስጥ እንዲገባ ሆኗል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ከዚህ ወገን የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል የተባለ ሲሆን ይህም ለወታደራዊ ሃይሉ ምላሽ አሰጣጥ መጨመር ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *