ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ፓርቲዎች ገለጹ::
አዲስ አበባ፣የካቲት 25፣ 2013 ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ፓርቲዎች ገለጹ:: በጋምቤላ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ምርጫው ያለንዳች እንከን እንዲሳካ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ፉክክር ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አመራሮቹ ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲ ጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክድር ላክባክ እንዳሉት ፤ ብልጽግና በክልሉ ከሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትብብር እየሰራ ይገኛል።
አሁን ላይም ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፣ በህዝብ ዘንድ ታአማኒና ተቀባይነት ያለው ሆኖ እን ዲጠናቀቅም በመስራት ላይ እንዳሉ ገልጸዋል።መጪው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍጹም ታማኒነት ያለው ሆኖ ፍፃሜውን እንዲያገኝ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ
ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ / ጋህነን/ ጸሐፊ አቶ ተዘራ ኃለማሪያም ናቸው።
በተወሰኑ ወረዳዎች ከግንዛቤ ማነስ ከሚታዩ ጥቃቅን ችግሮች በስተቀር በክልሉ እስካሁን ያለው ሂደት መልካም እንደሆነ ገልጸዋል። በቀጣይም ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲዎችም ሆኑ መላው የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን በመሆኑን ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ ተዘራ አሳስበዋል።