loading
ሚኒስቴሩ የኮቪድ -19 በሽታን ከመከላከል አንጻር ባለፉት 6 ወራት ዉጤታማ ስራዎችን ሰርቼያለሁ አለ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013 ሚኒስቴሩ የኮቪድ -19 በሽታን ከመከላከል አንጻር ባለፉት 6 ወራት ዉጤታማ ስራዎችን ሰርቼያለሁ አለ፡፡ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በ2013 በጀት አመት ባለፉት 6 ወራት የኮቪድ ወረርሺኝ ለመከላከል እንዲያግዝ በመላ ሀገሪቱ ከ74 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ መቻሉን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአማራ ክልል በአይነት እህል 1በንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና በቤት ዉስጥ ቁሳቁሶች ማሰባሰብ እና ድጋፍ ለሚያስፍልጋቸዉ ማድረስ ተችሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስተባባሪነት ከ38, ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንፅህና መጠበቂያና የምግብ ቁሳቁስ ተሰባስቧል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የተሰበሰበ ቁሳቁስ ወደ ገንዘብ ሲቀየር ከ31, ሚለዮን በላይ ሲሆን ይህም ቫይሱን ለመከላከል እንዲያስችል ለተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶች ዉሏል፡፡

ሚኒስቴሩ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በ6 ወራት ዉስጥ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ህፃናት ማሳደጊያ 5 መቶ ሺህ ብር የሚገመት የሳሙና፣ ሳኒታይዘር፣ የፊት መሸፈኛ ማስክ፣ የውሃ ታንከሮች ድጋፍ ማድረጉን በላከልን መረጃ ገልጿል፡፡ በደ ወራት የሚኒስቴሩ ስራዎች የግብዓቶች እጥረት፣ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ውስንነት፣ አጋጥሞኝ ነበር ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *