loading
አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር የበሽታው ስርጭት በአፍሪካ አነስተኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ በ47 የአፍሪካ ሀገራት በበሽታው የተያዙባቸው ዜጎች ሳምንታዊ አማካይ ቁጥር 73 ሺህ መድረሱ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ አህጉር የበሽታውን የስርጭት መጠን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ተናግሯል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የኮሮናቫይረስ ክትባት ተገኘ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ የስርጭት ሂደቱ ዘገየ በተባለበት ወቅት የቫይረሱ መስፋፋት አሳሳቢ አየሆነ መጥቷል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ በቫይረሱ በስፋት የተጠቁ ሀገራት በባዓል ጊዜ ሰዎች ተሰባስበው እንዳያከብሩ የእንቅስቃሴ እቀባዎችን እያጠናከሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አህጉር 60 በመቶ ለሚሆኑት ህዝቦቿን ክትባት ለማዳረስ ከ7 እስከ 10 ቢሊዮን ደላር ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት ይነገራል፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ሞሮኮና ግብፅ ክትባት የጀመሩ ሲሆን ዩጋንዳ፣ ኬንያና ናሚቢያ ኮቫክስ የተባለውን ክትባት እንዲመጣላቸው አዘዋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *