በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::በከተሞች ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡
ፕሬዝዳንቷ ይህን ያስታወቁት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች የሰላም ፎረም ላይ ነው፡፡”የፍትህና ተጠያቂነት መጓደል፣ የኑሮ ደረጃ ልዩነቶች፣ እንዲሁም ስራ አጥነት በከተሞች የሚስተዋሉ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው” ብለዋል፡፡ችግሮቹን ለመፍታት ከህዝቡ ጋር በግልጽ ውይይት መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡የከተሞች ሰላም ለሀገራችን ዘላቂ ልማት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በፖሊሲ ሊደገፍ እንደሚገባ አስታውቀዋል ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያዘጋጀውና “ከተሞችና ሰላም” በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ እየተካሄደ ባለው የከተሞች ፎረም ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።በፎረሙ ላይ “የከተሞች ሰላም ለሀገር ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጽኦ” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።