loading
በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታዉቀዋል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም በመጠናቀቁ እና የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል አከባበር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ከንቲባ አዳነች የመስቀል ደመራ በአል በሰላም እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ምእመናን እና ፀጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ባስቀመጠው የሰው ቁጥር መሰረት የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ ክብረ በዓል በመስቀል ደመራ በአል ዕለት በታየው የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ በሰላማዊ መንገድ መከበር ይኖርበታል ብለዋል። ኢሬቻ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የሰላም ፣ የእርቅ እና የመሰባሰብ በዓል መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ ፤የበዓሉ ተሳታፊዎችም ከአባ ገዳዎች የተላላለፈውን መልዕክት በመገንዘብ እንዲያከብሩ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *