loading
አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012 አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡አዲስ ሱዙኪ አልቶ 2020 ሞዴል መኪናም ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡አርትስ ቴሌቭዥን ባዘጋጀዉ የመጀመርያዉ ቨርችዋል ባዛር እየተካሄደ ሲሆን ለተመልካቾቹ እና ሸማቾችም በየቀኑ ከሞባይል አነስቶ ተለያዩ ሽልማቶችን በየቀኑ ይሸልማል፡፡

የአርትስ ቲቪ ስራ አስፈጻሚ አዜብ ወርቁ እንደገለጹት የመኪና ቶምቦላ ሽልማቱ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ያገኘ ሲሆን ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበርም የተዘጋጀ ነዉ፡፡የአርትስ ተመልካቾች በቶምቦላዉ ለመሳተፍ በእጅ ስልክ በቴሌግራም ማይ አሞሌን ሰርች በማድረግ በነጻ የቶምቦላዉን የእጣ ቁጥር ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል ፡፡

ለተጨማሪ መረጃም በ6294 የነጻ ስልክ መስመር በመደወል መረጃ ማግኝት ይቻላል ብለዋል፡፡

በባዛሩ በርካታ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተሳተፉበት ሲሆን፤ ባዛሩን በየቀኑ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አስከ 6 ሰዓት፤ ከሰዓት ደግሞ ከ10 ሰዓት እስከ 12ሰዓት በአርትስ ቴሌቭዥን ዩቲዩብ እና ፌስቡክ ገጾች እየቀረበ እንደሚገኝ ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *