loading
ቢሮዉ ለሞተር ሳይክሎች ከዚህ በኋላ ፍቃድ እንደማይሰጥ ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ15፣ 2012 ቢሮዉ ለሞተር ሳይክሎች ከዚህ በኋላ ፍቃድ እንደማይሰጥ ገለፀ::በአዲስ አበባ ከተማ በሞተር ሳይክሎች ላይ የወጣዉን መመሪያ በመጣስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሞተኞች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የ ከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡በከተማዋ ነዋሪ የነበሩና በሞተር ሳይክል ላይ ኑሮአቸዉን አድርገዉ ህጋዊ ለሆኑ 3600 የሚሆኑ ሞተረኞች ፋቃድ መስጠቱን ያስታወቀዉ ቢሮዉ ፋቃድ ከተሰጣቸዉ ዉጪ የሚንቀሳቀሱ ግን ንብረታቸዉ ተወርሶ ጉዳያቸዉ በህግ የሚታይ መሆኑን ገልፅዋል፡፡ቀደም ሲል ከትራፌክ መጨናነቅ ጋር ተያይዞ በዋናነትም የወንጀል መበራከትን ተከትሎ መመሪያ የወጣ መሆኑ የሚታወስ ሆኖ ሳለ አሁን ላይ ከከተማ ዉጪ ያሉ ታርጋዎችን በመጠቀምና በከተማዋ በመንቀሳቀስ ወንጀሎችን በማባባስ የሚገኙ ሞተረኞች እንዳሉ ማስተዋል ተችልዋል፡፡

የአስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፌ አቶ ስጦታዉ አካለ ይህን የሚያደርጉ አካለት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አሳስበዉ ከድርጊታቸዉ የማይቆጠቡ ካሉ ግን ንብረታቸዉ ተወርሶ ጉዳያቸዉ በህግ የሚታይ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ቀደም ብለዉ ፍቃድ ካገኙት ዉጪ ለጊዜዉ ከሚያስከትለዉ የትራፌክ መጨናነቅ አንፃርና እያስከተለ ካለዉ ቀዉስ አንፃርም ከዚህ በኋላ ፣ፍቃድ እንደማይሰጥ የገለፁት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስከያጅ አቶ አህመድ መሃመድ ናቸዉ፡፡በመሆኑም ድርጊቱን ከመከላከል አንፃር የሚመለከታቸዉ ሁሉ እንዲረባረቡና ህረተሰቡም በጥቆማ እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *