በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ;ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም መወሰኑን ዶክትር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል ተብሏል።