የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡ ቤተክርስትያንዋ ላደረገችዉ ድጋፍ በአማራ እና አፋር ክልል በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ 10 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰራጭ ነዉ፡፡ ለደቡብ ወሎ ዞን የተደረገውን 800 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ የሙቀት መለኪያ፣የምግብ ዘይት፣ዱቄትና የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሰቀቁሶችን የዞኑ ኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ተረክቧል፡፡በደቡብ ወሎ ዞን እስካሁን 102 ሺህ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ተለይቷል፡፡እስካሁንም በገንዘብ 29 ሚሊዮን ብር እና 4ሽህ800 ኩንታል እህል በዓይነት ተሰብስቧል፡፡
የቤተክርስቲያኗ የማዕከላዊ ሰሜን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ቄስ ዋኘው አንዳርጌ በአገር አቀፍ ደረጃ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን በጀት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ቤተክርስቲያኗ እየሰራች ነው ብለዋል፡፡በምስራቅ አማራና በአፋር ክልል ደግሞ በ120 ሚሊዮን ብር የምግብ ዋስትናና የማህበራዊ ልማት ስራዎች በመስራት ላይ መሆኗንም ጠቁመዋል፡፡አሁንም የተደረገው ድገፍ ኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቤተክርስቲያኗ ከማህበረሰቡና ከመንግስት ጎን በመሆን ወገናዊነቷን አሳይታለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የልማት ዳሬክተር የሆኑት አቶ አዲሱ አላምረው በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ ለማህበረሰቡ ከምታከናውነው የልማት ስራዎች በተጨማሪ ኮቪድ-19ን መንግስት ለመከላከልና ለመቆጣጠር
የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ 2ነጥብ2 ሚሊዮን ብር በሚሆን ወጪ ምግብ እና የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሰቀቁሶችን ለምስራቅ አማራና ለአፋር ክልል ድጋፍ ማድረጓን ሲገልፁ ወደፊትም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅና ሀብት በማፈላለግ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል፡፡