loading
ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የሚሳተፉበት ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የሚሳተፉበት ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ::መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የፊታችን እሁድ በአይነቱ ልዩ የሆነ  ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ መሆኑ ተገለጸመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ዲኤስቲቪ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ውስጥ የራሱን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ ቻናል 154  እንደሚተላለፍ ገልጿል፡፡ሆፕ ፎር አፍሪካ ኮንሰርት የተሰኘውን የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን እሁድ ግንቦት 23/2012 ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ ስለ ኮቪድ-19 ታላላቅ የአፍሪካ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ከሚያስተላልፉት መልክት ጋር ያቀርባል።

ይህ ኮንሰርት  በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ Africa Magic Family , Channel 154 ላይ የሚተላለፍ ሲሆን ታላላቅ የአፍሪካ ድምጻዊያንና ታዋቂ ግለሰቦችን ከቤታቸው የሚያሳትፍና ገቢው በመላው አፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ከፊት ለፊት ሆነው በመዋጋት ላይ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ ለማድረግ ይውላል።ለ3 ሰአታት በቀጥታ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ልዩ ኮንሰርት ታዋቂ የአፍሪካ ድምጻዊያንንና የተለያዩ ታዋቂና ተጽኖ  ፈጣሪ ግለሰቦችንም ያከተተ ይሆናል ተብሏል።ይህ በታላላቅ ኮኮቦች የተሞላው ኮንሰርት ታዋቂዎቹን  ቱ ባባ ፡ አኮቴ፡ ባንኪ ደብሊው፡ ቤቲ ጂ፡ ልጅ ሚካኤል እና ሌሎችንም ያከተተ ሲሆን፡ ሁሉም ከቤታቸው ሆነው  ለአፍሪካውያን ሁሉ የተስፋና የማበረታቻ  መልክቶች ያስተላልፋሉ::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *