loading
የአሜሪካ እና የኢራን ፍጥጫ የዓለምን መሪዎች አሳስቧል፡፡

የአሜሪካ እና የኢራን ፍጥጫ የዓለምን መሪዎች አሳስቧል፡፡

አሜሪካ በባህረ ሰላጤው አካባቢ የጦር ሀይሏን ማጠናከሯ እና ኢራን የአሜካን ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏ ውጥረቱን ይበልጥ አባብሶታል፡፡

ሩሲያ የነገሩ በነሻ አሜሪካ ናት ስትል ወቅሳለች፡፡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ሪያብኮቭ በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን የምትከተለው አካሄድ አደገኛ ነው ብለዋል፡፡

እንግሊዝ በበኩላ ከአሜሪካ ጋር ተከታታይ ንግግሮችን እያደረግን ነው፤ ግን ደግሞ ሁለቱም ወገኖች ነገሩን በሰከነ መንገድ ሊመለከቱት ይገባል ብላለች፡፡

የጀርመኗ ቻንለር አንጌላ ሜርክል ደግሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ሀይል መፍትሄ እንዳልሆነ ደጋግመው ሲናገሩ መስማታችን መልካም ነው፤ ቴህራንም ሀነች ዋሽንግተን ችግሩ እንዳይባባስ መስራት አለባቸው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም በቃል አቀባያቸው በኩል ባስተላለፉት መልእክት የሁለቱም ሀገራት ባለ ስልጣናት ሆደ ሰፊ መሆን አለባቸው ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *