loading
ኢ/ር ታከለ ኡማ በሰዓት 80ሺ ዳቦ የሚያመርት እና መቶ ግራም ዳቦ በ0.75 ሳንቲም ለሚያቀርብ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በሰዓት 80ሺ ዳቦ የሚያመርት እና መቶ ግራም ዳቦ በ0.75 ሳንቲም ለሚያቀርብ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው ከ4-6 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡

በከተማ ውስጥ ያለውን የዳቦ አቅርቦት ከፍ የሚያደርገው እና የዋጋ ንረቱን የሚያረጋጋው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ግንባታው ሲጠናቀቅ አንድ ዳቦ በ0.75 ሳንቲም ለህብረተሰቡ ያቀርባል፡፡

የመሠረተ ድንጋይ በማኖር ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር ከግል ባለሃብቱ ጋር በመተባበር ለህብረተሰቡ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን በዝቅተኛ ዋጋ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

በሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግንባታ የሚከናወነው ይህ የዳቦ ማምረቻ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለበርካታ የአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *