የግብፅ ፍርድ ቤት የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ከእስር እዲለቀቅ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡
የግብፅ ፍርድ ቤት የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ከእስር እዲለቀቅ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡
ከ2 ዓመታት በላይ በግብፅ እስር ቤት ያሳለፈው የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ሞሀመድ ሁሴን እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም አቃቤ ህግ ፍርዱ ትክክል አይደለም ብሎ ይግባኝ አቅርቧል፡፡
የጋዜጠኛው ጠበቃ ጣሂር አቡል ናስር ደንበኛቸው በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ጋዜጠኛው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2016 መደበኛ ክስ ሳይመሰረትበት ነው ወደ እስር ቤት የገባው፡፡
መቀመጫውን ኳታር ዶሀ ያደረገው አልጀዚራ “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” የሚል መሪ ሀሳብ ይዞ የጋዜጠኛ ሁሴንን መታሰር በመቃወም በተደጋጋሚ ግብፅን ሲወቅስ ነበር፡፡
ግብፅ ሁሴንን ያሰረችው የሀሰት ዜና በማሰራጨት እና ለብጥብጥ የሚያነሳሳ ዘገባ ሲያስተላልፍ አግኝቸዋለሁ ብላ ነው፡፡
የግብፅ መንግስት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2017 የትኛውም የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እነዳይዘግብ እገዳ መጣሉ ይታወሳል፡፡
መንገሻ ዓለሙ