loading
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ አውደ ጥናት ተካሂደ፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ አውደ ጥናት ተካሂደ፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አውደ ጥናቱን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የመሰረተ ልማትና ኢንድስትሪ ፓርኮችን በማስፋፋት በኩል ጥሩ እምርታ ብታስመዘግብም ፤ተቀጥረው የሚሰሩ በርካታ ሰራተኞች በሚከፈላቸው ደመወዝ ቅሬታ እንደሚያሰሙና መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን የሚጠይቁበት ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰን ውስብስብ በመሆኑና የአሰሪውም ሆነ የሰራተኛው እይታወች የተለያዮ በመሆናቸው መንግስት የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፍትሀዊ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
የውይይት አውደ ጥናቱም በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ በማዳበር ሀገራችን ለምትወስነው ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠን አከፋፈል ስርዓት የመሰረት ድንጋይ የሚጥል ጅማሮ እንደሚሆን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

የዓለም ስራ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር አሌክሶ ሙሲንዶ በበኮላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠንን ለመወሰን የጀመረው ስራ የሚበረታታና አድናቆት የሚቸረው መሆኑና ለዚህም የዓለም ስራ ድርጅት ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቆመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ታደለ ይመር በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮንፌዴሬሽኑ አባላት በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፅንስ አሳብ ላይ ችግር እንደሌለባቸውና ለሀገራችን ስራ መጎልበት ከሁላችንም የሚጠበቀውን ማድረግ እንደሚገባና ከዚህም በተጨማሪ ከዩንቨርስቲ ተምረው ለሚወጡም ሆነ ለሌሎች ሥራ አጥ ዜጉች ስራ መፍጠርና ወደ ስራ ማስገባት ሌላው አብይ ትኩረት ልንሰጠውና በጋራ ልንሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ጌታሁን ሁሴን በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠን የመወሰን ጉዳይ ወቅታዊ መሆኑንና ይህም ለኢንዱስትሪውና ለሠራተኛው የስራ መነቃቃት እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ የአሰራር ፍኖተ ካርታን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *