የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ግጥሚያዎች ዛሬ እና ነገ ምሽት ይከናወናሉ
የ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረግ፤ የእንግሊዙ ቡድን ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ባርሴሎናን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የካምፕ ኑ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ በካታላኑ ቡድን ድል አድራጊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ይህ ጨዋታ በባርሴሎና 3 ለ 0 ድል አድራጊነት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ዋንጫ ፍፃሜው ለማለፍ ሰፊውን ዕድል ይይዛል፡፡
ቀያዮቹ በታሪካቸው ለ9ኛ የአውሮፓ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታቸው ለመሻገር ግብ ሳይቆጠርበት በአራት ግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል፤ አሊያ 3 ለ 0 አሸንፎ ወደ መለያ ፍፁም ቅጣት ምት ሊያመራ ግድ ይለዋል፡፡
እንደ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ገለፃ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መሀመድ ሳላህ እና ሮቤርቶ ፊርሚኖ በጉዳት ምክንያት የማይኖሩ በመሆናቸው ለ19 ዓመቱ ወጣት ሪያን ብሬውስተር የመጀመሪያ የመሰለፍ ዕድል ሊሰጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ተጫዋቹ ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆነም ክሎፕ ተናግረዋል፡፡
አሰልጣኙ እጅ መስጠት የማይታሰብ ነው እያሉ ሲሆን ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ ለመሻገር ዕድሎች ካሉ ከመሞከር ወደኋላ እንልም ሲሉ አክለዋል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ ይጀመራል፡፡