loading
የቤኒን የምርጫ ውጤት ውዝግብ አስነስቷል፡፡

የቤኒን የምርጫ ውጤት ውዝግብ አስነስቷል፡፡

በቤኒን  የተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ውጤት ያልተዋጠላቸው ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው አንድም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ባልተሳተፈበት በዚህ ምርጫ በርካታ ዜጎች ደስተኞች አይደሉም፡፡

በዚህም ተነሳ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቦኒ ያይ ደጋፊዎች ጎዳና በመውጣት ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡

ሰልፈኞቹ ሌሊቱን ሁሉ ጎዳና ላይ  ያለ ምንም እንቅልፍ ያሳለፉ ሲሆን ጎማዎችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማቃጠልም መንገዶችን ዘግተው ታይተዋል፡፡

አሁን ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የነገሩ ቀስቃሽ ተደርገው ወደ እስር ቤት እንዳይላኩ ብዙዎቹ ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *