በቅርቡ የተቋቋመው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ
በቅርቡ የተቋቋመው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ ፡፡
ኮሚሽኑ በቀጣይ ጊዜያት እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ለማውረድ እንደሚሰራም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ወደ ስራ የገባው በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነተኛና ፍትህን መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈለጊ መሆኑን አምኖ ነበር ተብሏል፡፡
የእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት በመነሳት በቀጣይ በግጭቶቹ መንስኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ተነግሯል፡፡
የእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ ሰብሰቢ ብርሃን እየሱስ፣ የእርቅ ሂደቱ በባለሙያዎች የግጭቶችን ምንጭ በማጥናት ይቅር በማባባል በውይይት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰራ ነው ብለዋል፡፡
የሚቀርቡ አቤቱታዎችንም በባለሙያዎች ምርምራ በማድረግ የቅሬታዎችን መንስኤዎች በመመርመር ዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ፍትህ እንዲሰፍን ጥረት እንደሚደረግም በመግለጫው ተነግሯል፡፡ Picture @FBC