loading
የሚድሮክ ሄሊኮፕተር የመከስከስ አደጋ ደረሰበት፡፡

የሚድሮክ ሄሊኮፕተር የመከስከስ አደጋ ደረሰበት፡፡

ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ነው አደጋው የደረሰበት፡፡

ሪፖርተር እንደዘገበው ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ቢከሰከስም  በተሳፋሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት አልደረሰም፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ በሚድሮክ ቴክኖሌጂ ግሩፕ ሥር የሚተዳደር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት የዚሁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር በቦሌ አካባቢ መከስከሱ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *