ኡጋንዳ በቅርቡ ከስልጣን ለወረዱት ኦማር አል በሽር ጥገኝነት እሰጣለሁ አለች፡፡
ኡጋንዳ በቅርቡ ከስልጣን ለወረዱት ኦማር አል በሽር ጥገኝነት እሰጣለሁ አለች፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ለቀድሞው የሱዳን ፕሬዳንት ጥገኝነት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ያስታወቀ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ በአሁኑ ሰዓት የት እና በምን ሁኔታ ላይ እደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም፡፡
የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በበኩሉ አል በሽር ደህንነታቸው በሚጠበቅበት ስፍራ ላይ ናቸው ያለ ሲሆን ያሉበትን ቦታ ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል፡፡
የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦኬሎ ኦርየም አል በሽር የጥገኝነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ከሆነ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በኩል የሚታይ ይሆናል ብለዋል፡፡
አል በሽር ከደቡብ ሱዳን ጋር በተደረገው ስምምነት ትልቁን ድርሻ ተጫውተዋል ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ የእርሳቸውን የጥገኝነት ጥያቄ በአግባቡ ለማስተናገድ ፈቃደኞች ነን ማለታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የኡጋንዳ መንግስት በካርቱም የሚካሄደውን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ሂደቱን በቅርበት እንደሚከታተልም አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች ውጤታማ ልማት ማምጣት ያልቻሉት የስልጣን ቆይታቸው አጭር በመሆኑ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡
አብነት ታምራት