የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ አላማ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጎን ሊውለበለብ ነው ፡፡
የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ አላማ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጎን ሊውለበለብ ነው ፡፡
የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ አላማ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጎን እንዲውለበለብና የህብረቱ መዝሙር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀጥሎ እንዲዘመር ዝግጀት እየተደረገ ነው።
ጉዳዩን አስመልክቶ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅም ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
ይህን አስመልክቶም ጠቀሜታውንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነበተራትን ሚና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤትና በአዲስ አበባ ዩኒቨስርሲቲና አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል አስተባባሪነት የማስተዋወቂያ ዝግጅት ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እንዳሉት ይህ እንዲሆን የአፍሪካ መሪዎች በሀምሳኛው የህብረቱ ጉባኤ አባል ሀገራት የህብረቱን ሰንደቅ አላማ እንዲያውለበልቡና መዝሙሩንም እንዲያዘምሩ በአዋጅ መደንገጉን አውስተዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ እንደ አህጉር ብሎም በህብረቱ ከፍተኛ ሚና ያላት መሆኗን ገልጸው ሰንደቅ አላማውን ከማውለብለብና መዝሙሩን ከማዘመር ረገድ ግን ዘግይተናል ብለዋል።
ይህን ለማድረግም ጉዳዩን በህዝብ ዘንድ ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ሂሩት በቀጣይም በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣በመቀሌ፣ በባህርዳር፣ በሃሳብና ሌሎች ቦታዎች መሰል መድረኮች እንደሚኖሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እንደህብረቱ መቀመጫና በአፍሪካ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አገር ሁሉም ዜጋ ለህብረቱ ሰንደቅ አላማና መዝሙር ክብር ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡