loading
የ32ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ነገ ይጀመራል፡፡

ከሀገራት የማጣሪያ እና የወዳጅነት ጨዋታዎች መልስ የአውሮፓ ሀገራት የሊግ ውድድሮች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይካሄዳሉ፡፡

የ32ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀግብር መክፈቻ ጨዋታ በፉልሃም እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ቀን 9፡30 ሲል በክሬቨን ኮቴጅ ስታዲየም ላይ ይደረጋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12፡00 ላይ አምስት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬርን ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ቋሚ አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረው ማንችስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራርድ ዋትፎርድን ያስተናግዳል፡፡

ሌስተር ሲቲ በኪንግ ፓወር ከ ቦርንመዝ፣ በሴል ኽረስት ፓርክ ክሪስታል ፓላስ ከ ሀደርስፊልድ ታውን፣ በርንሊ በቱርፍ ሞር ከ ወልቨርሃምፕተን፤ ብራይተን በአሜክስ ከሳውዛምፕተን ይጫወታሉ፡፡

የማኑኤል ፔሌግሬኒው ዌስት ሃም ዩናይትድ ምሽት 2፡30 ከ ኢቨርተን በለንደን ስታዲየም ይገናኛል፡፡

በበነጋታው እሁድ ደግሞ ሁለት ግጥሚያዎች ሲደረጉ፤ የሳምንቱ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ጨዋታ ይደረጋል፡፡

የሊጉ አናት ላይ የሚገኘው የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ቶተንሃም ሆትስፐርን የሚገጥም ይሆናል፡፡ 

ቀን 10፡ 05 የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ወደ ዌልስ ምድር ተጉዞ ከካርዲፍ ሲቲ ጋር የሚፋጠጥ ይሆናል፡፡

ሰኞ የሳምንቱ ማሳረጊያ ጨዋታ ሲከናወን፤ አርሰናል ኢመሬትስ ላይ ምሽት 5፡00 ላይ የራፋኤል ቤኒቲዙን ኒውካስትል ዩናይትድ ያስተናግዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *