loading
440 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ፡፡

440 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳኡዲ አረቢያ መንግስትና ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 440 ኢትዮጵያዊያንን በራሳቸው ፈቃድ ከሳኡዲ አረቢያ እንዲመለሱ አድርጓል።

ዜጎቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይ አቶ አበበ መብራቱ እና የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ መረጃ በዚሁ ሳምንት በጂዛን ሳኡዲ አረብያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 600 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ በቀጣይ ቀናቶች ውስጥ ቁጥራቸው ወደ 500 የሚደርሱ ዜጎቻችን ከሳኡዲ አረቢያ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *