ሙሴቬኒ ለስድስተኛ ጊዜ በምርጫ ሊወዳደሩ ነው፡፡
ሙሴቬኒ ለስድስተኛ በምርጫ ሊወዳደሩ ነው፡፡
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በፈረንጆቹ 2021 ሀገራቸው ለምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ሆነው እንደሚቀርቡ ፓርቲያቸው ይፋ አድርጓል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ናሽናል ሬዚስታንስ ሙቭመንት ፓርቲ በራሳቸው ሰብሳቢነት ከተወያየ በኋላ ነው ሙሴቬኒ ለስድስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ ስምምነት ላይ የደረሰው፡፡
ሙሴቬኒ በአንድ ወቅት ለረጂም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚቆዩ መሪዎች ለአፍሪካ ችግር መንስኤዎች ናቸው ቢሉም በ2016 ለአምስተኛ ጊዜ ሲወዳደሩ ደግሞ ይሄን የማደርገው ገና ለሀገሬ ሰርቸ ያልጨረስኩት ስራ ስላለኝ ነው ብለዋል፡፡
የሰባ አራት ዓመቱ ሙሴቬኒ በ2017 የፕሬዝዳንቱ እድሜ ከ75 እንዳያልፍ የሚደነግገውን ህግ ከሻሩ በኋላ ነው ለመወዳደር የተዘጋጁት፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1986 ወደ ስልጣን የመጡት እና ሀገሪቱን ለ33 ዓመታት የመሩት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በ2021 ቢመረጡ ዩጋንዳን ለ40 ዓመት ያስተዳራሉ ማለት ነው፡፡
መንገሻ ዓለሙ