የቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ሁለት ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡
የቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ሁለት ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡
የ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የመጀሪያ ዙር ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት 5፡00 ላይ ይከናወናሉ፡፡
የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ወደ ጀርመን አምርቶ በቬልቲንስ አሬና ሻልከን ይገጥማል፡፡ በምሽቱ ግጥሚያ የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ሌሮይ ሳኔ የቀድሞ ክለቡን የሚገጥም ይሆናል፡፡
ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ አናት ላይ ሲገኝ በአንፃሩ ሻልከ በቡንደስሊጋው 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በምሽቱ በጉጉት የሚጠበቀው ሌላኛው ጨዋታ ደግሞ አትሌቲኮ ማድሪድ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከዩቬንቱስ የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው፡፡ ሮናልዶ እና ዲባላ በአሮጊቷ በኩል እንደሚጣመሩ ተነግሯል፡፡
ይህ ግጥሚያ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ያለማንሳት ዕድል ባለቸው ሁለት ቡድኖች መካከል የሚከናወን ነው፡፡