loading
ማንችስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡

 

 

ትናንት ምሽት ኤምሬትስ ኤፍኤ ዋንጫ የአምስተኛ ዙር ጨዋታዎች የመጨረሻ ግጥሚያ ተደርጓል፡፡ ወደ ምዕራብ ለንደን የተጓዘው ማንችስተር ዩናይትድ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ቼልሲን በሜዳውና ደጋፊው ፊት 2 ለ 0 በመርታት የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚነቱን አረጋግጧል፡፡

 

 

ለኦሌ ጉናር ሶልሻዬሩ ቡድን ዳግም ወደ አሸናፊነት መመለስ ግብ አስቆጣራዊቹ አንደር ሄሬራ እና ፖል ፖግባ ሲሆኑ ፖግባ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡ ዩናይትድ በቻምፒዮንስ ሊጉ የደረሰበትን ሽንፈትም ማካካስ ችሏል፤ አሁን ቡድኑ በሶልሻዬር ስር መሰልጠን ከጀመረ 13 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን በ11ዱ ላይ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

 

 

የማንችስተሩ ቡድን በአንድ የውድድር ዓመት ሁለቱን የለንደን ክለቦች አርሰናልና ቼልሲ ያሸነፈ ብቸኛው ክለብ ሲሆን ቀያይ ሰይጣኖቹ ከዚህ ቀደም በ1998-99 የውድድር ዘመንም ይሄንን ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡

 

 

ቼልሲ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የአሰልጣኙ ማውሪዚዮ ሳሪን የስታንፎርድ ብሪጅ ቆይታ እያፋጠነው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

 

 

ሳሪ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ግራ የገባው አግር ኳስ ነበር የተጫወትነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *