አትሌት ሳሙኤል ተፈራ የ1500 ሜ ዓለም የቤት ውስጥ ክብረወሰንን አሻሻለ ።
አትሌት ሳሙኤል ተፈራ የ1500 ሜ ዓለም የቤት ውስጥ ክብረወሰንን አሻሻለ ።
ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ እንግሊዝ በርሚንግሃም ላይ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድርን የዓለም ክብረወሰን በመስበር ጭምር በቀዳሚነት አጠናቅቋል ።
ሳሙኤል የገባበት ጊዜ 3:31.04 ሲሆን ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ3:31.58 ሰዓት ሁለተኛ ሁኗል ።
ሳሙኤል ያስመዘገበው ሰዓት ፤ በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ከ22 ዓመታት በፊት 1997 ላይ ሞሮኳዊው አትሌት ሂሻም ኤል ጉሩጅ በ3:31.18 ጊዜ ይዞት የነበረውን ነው ።
ከዉድድሩ አስቀድሞ የማሸነፍ ግምቱ ተስጥቶት የነበረው ለዮሚፍ ነበር።
ምንጭ፦አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ