loading
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርና የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ተወያዩ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ማውረን አቺንግ ጋር በሁለትዮሽ የትብብር ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

ምክክራቸውም ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ በሚችሉበት ሁኔታ፣ እንዴት በህጋዊ መንገድ ለሥራ መጓዝ እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠርና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሕጋዊ የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን የማጠናከር ፣ በውጭ አገራት ለሥራ የሚሰማሩ ዜጎች ተገቢው ስልጠና ማግኘት የሚችሉባቸውን ተቋማት የማደራጀት፣ በውጭ አገር ስራና ሠራተኛን የማገናኘት ተግባር በስነ-ምግባር የሚመራበትን ስርዓት የመፍጠር፣ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችንና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በጋራ ማከናወን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም ተመካክረዋል ተብሏል።
በተጨማሪም ከስደት ተመላሾችን የማቋቋም ሥራ በተሻለ ሁኔታ ማከናወን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሚኒስትሯና የአለም የፍልሰት ድርጅት ተጠሪዋ ጋር መክረዋል፡፡
ከሚኒስቴሩ በተገኘው መረጃ መሰረት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ህጋዊ የውጭ አገር ስራ ስምሪትን ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት ለሚሰጠው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የሁለቱ ተቋማት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *