loading
ለሪልስቴት ልማት መሬት ወስደው ወደተግባር ያልገቡት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

ለሪልስቴት ልማት መሬት ወስደው ወደተግባር ያልገቡት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው ተባለ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳስታወቀው በከተማዋ ውስጥ በሪልስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን የግንባታ ሁኔታ እና ህጋዊነት የሚያጠና ግብረሃይል አዋቅሮ የዳሰሳ ጥናት ሲያከናውን ቆይቷል።

 

በዚህም ግብረሃይሉ በፋይል ፣ የግንባታ ሳይት ላይ ጉብኝት በማድረግ እና መጠይቆችን በመጠቀም የሪልስቴቶቹን የህግ አግባብነት ፣ የሊዝ ውል እና የግንባታ ደረጃ ሲያጣራ ቆይቶ የደረሰበትን የኦዲት ሪፖርት በዛሬው ዕለት ለከተማ አስተዳደሩ አቅርቧል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ህጋዊ አግባብነት በሌላቸው እና ግንባታ ባልጀመሩ የሪልስቴት ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ወስኗል፡፡

 

በዚህም መሬት ወስደው ግንባታ ባልጀመሩ እና መሠረት ብቻ አውጥተው ወደ ግንባታ ያልገቡ የሪልስቴት ድርጅቶች ይዞታ ተነጥቆ ወደ መሬት ልማት ባንክ ገቢ እንዲደረግ እና ተመላሽ የተደረገውም መሬት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ላይ እንዲውል ወስኗል ብሏል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *