loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ወደ ሊጉ መሪነት ሲመጣ፤ ኢትዮጵያ ቡና ተሸንፏል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ወደ ሊጉ መሪነት ሲመጣ፤ ኢትዮጵያ ቡና ተሸንፏል

የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች (15ኛ ሳምንት) ሁለት ግጥሚያዎች ዛሬ ተካሂደዋል፡፡

ድሬዳዋ ላይ መቐለ 70 እንደርታን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከነማ ሲመራ ቆይቶ የ2 ለ 1 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ለሰሜኑ ቡድን አማኑኤል ገብረሚካኤልና ሙሉጌታ ወልደ ጊዮርጊስ ከመረብ ሲያገናኙ፤ ራምኬል ሎክ ለምስራቁ ቡድን የማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ይህን ተከትሎ የትግራዩ ተወካይ መቐለ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እያለው የሊጉን መሪነት በ29 ነጥብ ተረክቧል፡፡

ሌላኛው ግጥሚያ ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲም የተከናወነ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች፤ በመቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የሚመራውን የክለቡን ቦርድ ይቅርታ ተጠይቀዋል፡፡

መከላከያ ባለሜዳ ሁኖ በገባበት ጨዋታ የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን፤ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በመርታት ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል፡፡ የጦሩ ቡድን አሸናፊ ሁኖ እንዲወጣ ያስቻለችውን ግብ ደግሞ ፍቃዱ ዓለሙ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

ቡናዎች ጨዋታው ገና በተጀመረ በ5ኛው ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም አቡበከር ናስር ወደ ግብ የላካትን ኳስ የመከላከያው ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ በቁጥጥሩ ስር አውሏታል፡፡

ቡናዎች የዛሬውን ጨምሮ በአራት የሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት  አስተናግደዋል፡፡በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥም ወደታች እየተንሸራተቱ ሲሆን በ22 ነጥብ 8ኛ ላይ ይገኛሉ ፡፡

ሊጉን መቐለ በ29 ነጥብ ሲመራ፤ ሲዳማ ቡና በ27 ሁለተኛ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ሀዋሳ እና ፋሲል ከነማ በእኩል 24 ነጥቦች አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጥዋል፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ አና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ተገኝተዋል፡፡

የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በ11 ጎሎች ሲመራ፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ 70 እንደርታ በ10 ጎሎች ይከተላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *