loading
ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ስኬት መንግሥት ያቅሜን ሁሉ ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡

ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ስኬት መንግሥት ያቅሜን ሁሉ ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡ በህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤት የተሰየሙት የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት እንዲተዋወቁ አድርገዋል።

በትዉዉቁ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ተልዕኮ ስኬት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀዋል።

ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተዉ የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምከንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም፤ እውነት እና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅን ለማውረድ እንዲያግዝ የተቋቋመው ነዉ፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለእርቀ ሰላም ኮሚሽኑ 41 አባላትን መሾሙም ይታወሳል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *