loading
ከህንድ የተሰማው ዜና አረንጓዴ ሻይ ገዛሁ ብለው በጫት ቅጠል እንዳይታለሉ ይላል፡፡

ከህንድ የተሰማው ዜና አረንጓዴ ሻይ ገዛሁ ብለው በጫት ቅጠል እንዳይታለሉ ይላል፡፡

የህንድ ፖሊስ ከአሁን በፊት ገጥሞት በማያውቅ ዘዴ ሊያልፍ የነበረን እፅ በደልሂ አየር መንገድ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግሯል፡፡

የአረንጓዴ ሻይ ምልክት የተለጠፈባቸውን የፕላስቲክ ከረጢቶች ሲመለከት ጥርጣሬ የገባው ፖሊስ እሽጎቹን ሲመረምራቸው በውስጣቸው የያዙት በደረቁ የተዘጋጀ ጫት ሆኖ አግኝቶታል ፡፡

አረንጓዴ ሻይ የሚል የምርት መለያ ተለጥፎበት አየር መንገዱን ሊያልፍ ሲል  የተያዘው የደረቀ ጫት መጠኑ 600 ኪሎ ግራም ሲሆን 2.4 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሏል፡፡

ሂንዱስታን ታይምስ እንደዘገበው በፕላስቲክ ከረጢቶች ታሽጎ በፖሊስ የተያዘው ይህ ደረቅ ጫት የገዥዎችን ፍላጎት የሚቀሰቅስ በብርጭቆ የተቀዳ የሻይ ምስልም ታትሞበታል፡፡

ጫት በህንድ ሳይኮትሮፒክ ከሚባለው የአደንዛዥ እፅ ስለሚመደብ በይፋ እንዳይዘዋወር እና  ጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለ ተክል ነው፡፡

ከዝውውሩ ጋር በተያያዘ ሁለት ኢትዮጵያዊያን እና አንድ የካርጎ ተርሚናል ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ተብሏል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *