loading
.አሜሪካ የሜክሲኮ ድንበር ላይ ተጨማሪ ወታደሮችን ልትልክ ነው

.አሜሪካ የሜክሲኮ ድንበር ላይ ተጨማሪ ወታደሮችን ልትልክ ነው

የአሜሪካ  መከላከያ ሚኒስትሩ ፓትሪክ ሸንሃን  እንዳስታወቁት  አሜሪካ ከሜክሲኮ ጋር በምትዋሰንበት  ድንበር ላይ ከ3 ሺህ በላይ ተጨማሪ ወታደሮችን ልትልክ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ወታደሮች በቦታው ለ3 ወራት የሚቆዩ ሲሆን ከተለያዩ  ሀገራት ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚሞክሩ ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያግዛሉ ተብሏል።

ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ በሜክሲኮ ድንበር ላይ ልትልክ ያሰበችው የወታደሮች ቁጥር ሀገሪቱ በአካባቢው ያሰማራችውን የወታደሮች ቁጥር ከ4 ሺህ በላይ ያደርገዋል ፡፡

ፕሬዚዳንት  ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በሜክሲኮ ድንበር አድርገው ወደ አሜሪካየሚገቡ ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመከላከል ድንበሩ ላይ ትልቅ ግንብ አጥር መገንባትን መፍትሄ አድርገው ማቅረባቸው ይታወሳል ።

ፕረዝዳንቱ በድንበሩ ላይ እንዲገነባ ያሰቡትን  ግንብ ለማስጀመር በጀት ቢያቀርቡም ግንባታው ያልተጀመረው  በዲሞክራቶች በኩል  በቀረበባቸው ተቃውሞ ነበር፡፡

በቅርቡም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግንቡን ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ ለማግኘት የሚያስችል አዲስ  እቅድ እንደሚያቀርቡ  ይጠበቃል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *