loading
በኮፓ ዴል ሬይ ደግሞ ሪያል ማድሪድ ግማሽ ፍፃሜውን ተዋህዷል

በኮፓ ዴል ሬይ ደግሞ ሪያል ማድሪድ ግማሽ ፍፃሜውን ተዋህዷል

ትናንት ምሽት ጅሮና በስታዲዮ ሙኒሲፓል ዴ ሞንቲሊቪ ሪያል ማድሪድን አስተናግዶ የ3 ለ 1 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ በአጠቃላይ ማድሪድ 7 ለ 3 በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡

ፈረንሳያዊው ካሪም ቤንዜማ ሁለት ግቦችን ለሎስ ብላኮስ ሲያስቆጥር ቀሪዋን ማርኮስ ዮሬንቴ አክሏል፡፡

ቤንዜማ ትናንት ምሽት ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ለማድሪድ በ446 ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን በአጠቃላይ ወደ 209 ያደረሱ ሲሆን በክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መዝገብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጠውታል፡፡

ፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ451 ጎሎች ቀዳሚ ሲሆን፤ ራውል ጎንዛሌዝ በ323 ሁለተኛ፤ አልፍሬዶ ዲ ስቲፋኖ በ308 ጎሎች ሶስተኛ፤ ሳንቲያና በ290፣ ፌሬንች ፑሽካሽ በ242 አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ፤ ቤንዜማ በ209 ስድስተኛ እንዲሁም ሁጎ ሳንቼዝ በ208 ጎሎች ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ማድሪድ ግማሽ ፍፃሜውን አስቀድመው ከተቀላቀሉት ቫሌንሲያ፣ ባርሴሎና እና ሪያል ቤቲስ ክለቦች የተዋሀደ ሲሆን ዛሬ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ድልድል ይፋ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *