loading
የ5ኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ የዕጣ ድልድል ዛሬ ይፋ ይደረጋል

የ5ኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ የዕጣ ድልድል ዛሬ ይፋ ይደረጋል

የ2018/19 የአራተኛ ዙር ግጥሚያዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተካሂደው፤ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ቡድኖች በአብዛኛው ተለይተዋል፡፡

ትናንት ሁለት ጨዋታዎች ሲከናወኑ በለንደን ደርቢ ቶተንሃም ወደ ሴል ህረስት ፓርክ ስታዲየም አቅንቶ የ2 ለ 0 ሽንፈት ተከናንቦ ተመልሷል፡፡ ዊክሃም እና ቶውንሰንድ ለሮይ ሁድሰን ቡድን አስቆጥረዋል፡፡

ቼልሲ ደግሞ በስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ሸፊልድ ወንስደይን 3 ለ 0 በመርታት ማውሪዚዮ ሳሪ በተከታታይ ሀለተኛ አስፈላጊ ድል አሳክተዋል፡፡

በጨዋታው አዲሱ ፈራሚ ጎንዛሎ ሂግዌን የመጀመሪያ ጨዋታውን ተሰልፎ ያደረገ ሲሆን ብራዚላዊው ዊሊያን በጨዋታና በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ከመረብ ሲያገናኝ ቀሪዋን በጥር የተጫዋቾቸ ዝውውር መስኮት ስሙ ከባየርን ሙኒክ ጋር የተያያዘው ወጣቱ ካሉም ሁድሰን-ኦዶይ አስቆጥሯል፡፡

ወደ አምስተኛው ዙር ያለፉ ቡድኖችን ስንመለከት ማንችስተር ዩናይትድ፣ ብሪስቶል ሲቲ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ደርቢ ካውንቲ፣ ዶንካስተር ሮቨርስ፣ ዋትፎርድ፣ ስዋንሲ ሲቲ፣ ዊምብልደን፣ ሚልወል፣ ቼልሲና ክሪስታል ፓላስ ሲሆኑ ሽረውበሪ/ወልቭስ፣ ፖርትስማውዝ/ኪው.ፒ.አር፣ ሚድልስብራ/ኒውፖርት፣ ብራይተን/ዌስት ብሮሚች አልቢዮን የመልስ ግጥሚያዎች ተካሂደው አሸናፊው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ቡድኖችን ይቀላቀላሉ፡፡

የኤምሬት ኤፍ ኤ ዋንጫ አምስተኛው ዙር የዕጣ ድልድል ዛሬ ይፋ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *