loading
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው። ጠ/ሚሩ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፤ የሚመደቡባቸውን አገራት ፖሊሲ የመገንዘብና በአገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት የማስጠበቅ ሚና እንዳላቸው አስታውሰዋል። ውይይቱም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውስጥ የተደረጉትን ለውጦች ለመገምገም ያቀደ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *