loading
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው

የማዕከላዊ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሜሪ ኖኤል ኮዬራ ሩሲያ በሀገራችን  የጦር ሰፈር ለመገንባት ያቀረበችውን ጥያቄ በመልካም ጎኑ ነው የምናየው ብለዋል፡፡

ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ሩሲያ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለማሰልጠን ሙያተኞቿን ስትልክ በመርህ ደረጃ በሀገሪቱ የጦር ሰፈር ለመገንባት የሚያስችላትን ስምምነት አድርጋለች ፡፡

እስካሁን ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ባንወያይም ወደፊት የሁለቱም ሀገራት ባለ ስልጣናት ተገናኝተው ለመመካከር ዝግጁ ናቸው ነው ያሉት የመከላከያ ሚኒስትሯ ፡፡

መከላከያ ሚኒስትሯ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረትም ሂደቱን ለማገዝ ፍላጎት ስላለው ከባለስልጣናቱ ጋር የሚወያይበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡

ሩሲያ እና ቻይና በአፍሪካ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በዓይነ ቁራኛ የምትከታተለው አሜሪካ ግን   ነገሩን አፍሪካዊያንን በመደለል የሚደረግ ሸፍጥ ስትል አጣጥላዋለች፡፡

የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሩሲያ እና ቻይና አፍሪካ ውስጥ ስግብግብነት እያጠቃቸው ነው በማለት ነው ትችታቸውን የሰነዘሩት፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝባቸው በሩሲያ ላይ እምነት ስላለው በጋራ መስራታቸው ወደፊት መልካም አጋጣሚዎች  ይፈጠራሉ  የሚል ተስፋ እንዳላቸው  ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *