loading
የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜር በዚህ ወር መጨረሻ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተባለ፡፡

የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜር በዚህ ወር መጨረሻ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ይዘው የሚመጡት ፕሬዚዳንት ስቴይነሜር ከአቻቸው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትትንም ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

ከ100 ዓመታት በፊት በ1905 ኢትዮጵያና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩ ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ፣ በግብርናና በኢንቨስትመንት መስክ በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

35 የሚሆኑ የጀርመን ኩባንያዎች፤ በአበባ ልማት ዘርፍ ላይ በኢትዮጵያ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *