loading
የኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት የመነሻ ደመወዝ መጠን 1000 የሣዑዲ ሪያል እንዲሆን ከመግባባት ተደረሰ።

የኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት የመነሻ ደመወዝ መጠን 1000 የሣዑዲ ሪያል እንዲሆን ከመግባባት ተደረሰ።

የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከሳዑዲ አረቢያ አቻቸው አሕመድ ቢን ሱለይማን አል-ራጂ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል የተፈረመውን የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት ተግባራዊ በሚሆንበት ዙሪያ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ወደ ሳውዲ የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች መነሻ ደሞዝ  1000 የሣዑዲ ሪያል እንዲሆን  እና የሠራተኛውና የአሰሪው መብት በሚጠበቅበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ተደርሷል።

ከውይይቱ በኋሏም የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የሠራተኛና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብዱላህ አቡስነይን መግባባት የተደረሰባቸውን ዐብይ ነጥቦች የያዘ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መረጃ መሰረት ዝርዝር የሠራተኛ ስምምነት አተገባበር ጉዳይ የሚመለከተውን የሠራተኛ ቅጥር ሞዴል በቀጣይ ሁለቱ መንግስታት በኤምባሲዎቻቸው በኩል የሰነድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 በሪያድ  በሁለቱ አገራት መካከል የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡

ምንጭ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *