loading
የኢትዮጵያ የሀኪሞች ቡድን በኤርትራ ላደረገው ጉብኝት እና ለተሰሩት ስራዎች ኤርትራ ምስጋና አቀረበች

የኢትዮጵያ የሀኪሞች ቡድን በኤርትራ ላደረገው ጉብኝት እና ለተሰሩት ስራዎች ኤርትራ ምስጋና አቀረበች
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የተሾሙትን የኤርትራውን አምባሳደር ሰመረ ርዕሶምን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው አምባሳደሩ የኤርትራን ምስጋና ያቀረቡት።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የኢትዮጵያ የሀኪሞች ቡድን በኤርትራ ላደረገው ጉብኝት እና ለተሰሩት ስራዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለሁለቱ አገራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር ቀጣይነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሂሩት በውይይታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነትቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረቱ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡

በተለይም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን አሁን ካለበት ወደተሻለ ከፍታ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *