loading
የአውሮፓ ህብረት እስራኤል በጋዛ ትምህርት ቤቶችን ማፍረሷን እንድታቆም አሳሰበ

አርትስ 12/04/2011

ሰሞኑን ዌስት ባንክ ውስጥ ሲሚያ በተባለች መንደር የሚገኝ ትምህርት ቤት በእስራኤል ባለስልጣናት ትእዛዝ ፈርሷል፡፡

በዚህም ምክንያ በርካታ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ቤት ውስጥ መዋል አልያም መጠለያ በሌለው ቦታ እንደነገሩ ፊደል ለመቁጠር ተገደዋል፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል በአወሮፓ ህብረት የማእከላዊ ጋዛና ኢየሩሳሌም ልዩ ልኡክን ጠቅሶ  እንደዘገበው በ2018 ብቻ እስራኤል አምስት ትምህርት ቤቶችን አፍርሳለች፡፡

ሌሎች ትምህርት ቤቶች ደግሞ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳያገኙ የተገጠመላቸውን በፀሀይ  የሚሰራ የሀይል ምንጭ አቋርጣባቸዋለች፡፡

የአውሮፓ ህብረት በሪፖርቱ እንዳስታወቀው በኣካባቢው ሌሎች 50 ትምህርት ቤቶች ስራቸውን እንዲያቆሙ እና በእስራኤል ባለስልጣናት እንደሚፈርሱ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል፡፡

እነዚህ ትምህርት ቤቶች እንደተባለው የሚፈርሱ ከሆነ አምስት ሺህ የሚሆኑ የጋዛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የትም ለመዋል ይገደዳሉ ፡፡

ህብረቱ በመግለጫው እስራኤል የራሷን ዜጎች ለማስፈር በፍልስጤማውያን ላይ የምትፈፅመውን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ተግባር ቆም ብላ እንድትፈትሽ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ህብረቱ አክሎም እስራኤል ያፈረሰቻቸውን ትምህርት ቤቶች መልሳ የመገንባት እና ህፃናቱን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ሀላፊነት አለባት ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *