loading
የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት በስደተኞች አያያዝ ላይ አዲስ ስምምነት አደረጉ

የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት በስደተኞች አያያዝ ላይ አዲስ ስምምነት አደረጉ

አርትስ 02/04/2011

ስደተኞችን በተመለከተ አሁንም የዶናልድ ትራምፕና ተከታዮቻቸው አቋም በመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል  ከሚመራው ስብስብ ጋር መቀራብ አልቻለም፡፡

ሞሮኮ ባስተናገደችው ጉባኤ ላይ የተገኙ የ164 ሀገራት መሪዎችና ተወካዮቻቸው ለስደተኞች በየመዳረሻቸው ተገቢው ጥበቃ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህን ስምምነት የፈረሙ ሀገራት ቃላቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሌሎችም የነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ለማሳመን እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ አሁንም የስደተኞች ጉዳይ ግድ እንደማይሰጣት አረጋግጣለች፡፡ እንዲያውም አዲሱን ስምምነት የተባበሩት መንግስታት በየሀገራቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ  ያሳየበት ብላዋለች፡፡

አውስትራሊያ፣ ላቲቪያ፣ ስትሪያ፣ ቸክ ሪፓብሊክ፣ ሀንጋሪ፣ ቺሊ፣ ዶሚኒካ ሪፓብሊክ ፖላንድና ስሎቫኪያ  የአሜሪካን አቋም በመደገፍ ስብሰባውን ሳይታደሙ ቀርተዋል፡፡

ቡልጋሪያ፣ ኢስቶኒያ፣ ጣሊያን፣ እስራኤል፣ ስሎቬኒያና ስዊዘርላንድ ደግሞ ለመወሰን ተቸግረናል በማለት ሳይስማሙም ሳይቃወሙም  ቀርተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲሱን ስምምነት በፈረንጆቹ ታህሳስ 19 ኒው ዮርክ ላይ በይፋ የሚያፀድቀው ሲሆን  ለውሳኔ ያቅማሙ እና የተቃወሙ ሀገራት ሀሳባቸውን ይቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አንዳንድ ወገኖች ግን ስምምነቱ የማስገደድ ሀይል ስለሌለው አሁንም ሀገራቱ በሀላፊነት ስሜት ይተገብሩታል የሚል እምነት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *