loading
አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደረገ

አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደረገ

አርትስ 26/03/2011

 አውሮፕላኑ 3 ሰዓት በረራ ካደረገ በኋላ ከጉዞው ተመልሶ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት እንዲያርፍ የተደረገው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠረች ግለሰብን ለመያዝ ሲባል ነው።

የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ  በረራ ከመጀመሩ በፊት አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ ያለመፈተሽ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ቻይና ለምትጓዝ አንዲት ሴት ከፍተኛ መጠን ያለው የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶችን ለማቀበል ሲሞክር ተደርሶበት ነበር።

ሻንጣው ሲፈተሽም በውስጡ 6 ሺ 170 ፓውንድ፤ 33 ሺ 115 ዩሮ እና 1 ሚሊዮን 264 ሺ 975 የኢትዮጵያ ብር በመገኘቱ ሰራተኛው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ገንዘቡን ተቀብላ ወደ ቻይና የምትወስደው ግለሰብ ግን በረራ በመጀመሯ እሷን ለመያዝ የጫናት አውሮፕላን ከ3 ሰዓት በረራ በኋላ ዳግም ተመልሶ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲያርፍ ተደርጓል።

በዚህ መልኩም ግለሰቧ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንድትውል ተደርጓል ብሏል ገቢዎች ሚኒስቴር።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *