loading
የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን አቶ ተፈራ መኮንንን የኮሚሽኑ ዋና ጸሃፊ አድርጎ መረጠ

የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን አቶ ተፈራ መኮንንን የኮሚሽኑ ዋና ጸሃፊ አድርጎ መረጠ

አርትስ 25/03/2011
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የነበሩት አቶ ተፈራ መኮንን የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ጸሀፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ድርጅቱ ትናንት በዛምቢያ ሊቪንግስተን ውስጥ ባደረገው ስብሰባ ኢትዮጵያ በዕጩነት ያቀረበቻቸውን አቶ ተፈራ መኮንን መርጧል፡፡

አቶ ተፈራ መኮንን በአቪዬሽን ስራ የ37 ዓመት ልምድ ያላቸው ሲሆን በኬኒያ ናይሮቢ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ፕሮጀክት ማኔጀር እንዲሁም በአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ትራንስፖርት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡

በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽኑ ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ በመሆንም በካናዳ ሞንትሪያል ለ8 ዓመታት ያክል ሰርተዋል፡፡

የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን እ.ኤ.አ. በ1964 በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጉባኤ የተቋቋመ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ስራውን የጀመረው በ1969 ነው፡፡ የድርጅቱ መቀመጫም በሴኔጋል ዳካር ከተማ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *