loading
ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የሳምንቱ ማብቂያ ድሎቻቸው

ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የሳምንቱ ማብቂያ ድሎቻቸው

አርትስ ስፖርት 24/03/200

ቅዳሜ እና እሁድ ላይ በርካታ የአለም የጎዳናና የማራቶን ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል ተንበሻብሸዋል፡፡

በስፔን የቫሌንሽያ ማራቶን በወንድ 1ኛ ልኡል ገ/ስላሴ 2:04:31፣ 4ኛ ፀጋዬ ከበደ፤ በሴቶች 1ኛ አሸቴ በከር 2:21:14፣ 3ኛ ትንቢት ግደይ 2:23:37፣ አበሩ መኩሪያ 4ኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል፤

በጃፓን ፎኮካ ማራቶን በወንድ 1ኛ የማነ ጸጋዬ በ2:08:54 ሲያሸንፍ፤ በማካዎ ማራቶን – በሴቶች ሒሩት አለማዬሁ በ2:38:20 1ኛ በመውጣት ባለድል ሆናለች፡፡

በህንድ ፑኔ ማራቶን በወንዶች 1ኛ አጥላው ደበበ 2:17:23፣ 2ኛ ተሸመ ጌታቸው 2:18:01፣ 3ኛ አቤል አሰፋ 2:18:37 ተከታትለው ሲገቡ በሴቶች ደግሞ 2ኛ አስቴር መኮንን 2:51:18፣ 3ኛ ስመኝ ጥላሁን 2:52:40 በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ በቻይና SCO ኩንሚንግ ማራቶን – በወንድ 2ኛ በቀለ ቤኛ 2:20:56፣ 3ኛ ሐጎስ ገ/መስቀል 2፡21.08፤ በሴት 1ኛ ፀሐይ ገ/ክርስቶስ 2፡35.00 በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ በፑኔ ግ/ማራቶን በወንድ 1ኛ ጋዲሳ ጣፋ 1፡04.24፤ በሴት 1ኛ ድርቤ ገዝሙ 1፡19.10 በመውጣት ቀዳሚ ሆነዋል፡፡

በኔዘርላንድ ሞንትፌርላንድ 15 ኪሜ – በወንድ ሰለሞን በሪሁ 2ኛ በ43፡21፣ 7ኛ አንተንአየሁ ዳኛቸው፣ 9ኛ ታደሰ ተስፋሁን፤ በሴት 2ኛ በቀለች ጉደታ 49፡19 በመሆን ውድድሩን ሲፈፅሙ፤  በስፔን ቫሌንሺያ 10 ኪሜ ወንድ 2ኛ ኃይማኖት አለው 28፡43፤ በሴት 1ኛ ጽጌ ኃ/ስላሴ 32፡03 አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በሌሎች ርቀቶች ኮርስ ዲላኢስካላዴ (7.32 ኪሜ) ጀኔቫ ስዊዘርላንድ በሴት 1ኛ ሔለን በቀለ 23፡52 በወንድ 9ኛ ተሾመ ዳባ በመውጣት ውድድራቸውን ፈፅመዋል በማለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃውን ለአርትስ አድርሷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *