loading
የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ተቀናቃኞቻቸውን ሳይፈቱ ለምርጫ ተዘጋጅተዋል

የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ተቀናቃኞቻቸውን ሳይፈቱ ለምርጫ ተዘጋጅተዋል

አርትስ 23/03/2011

ሴኔጋል በመጭው የካቲት ወር በምታደርገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ለሁለተኛ ጊዜ ለመወዳደር ተዘጋጅተዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ዳግም ከተመረጡ በሀገራቸው ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ የተሻለ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

ይሁንና ፕሬዝዳናቱ ዋነኛ ተቃናቃኞቻቸውን እስር ቤት ካስገቡ በኋላ ምርጫውን በበላይነት ለማሸነፍ መዘጋጀታቸው እያስተቻቸው ይገኛል፡፡

በውጭ ጉዳይ  የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የነበሩት ካሪም ዋዴ እና የቀድሞው የዳካር ከንቲባ ካሊፋ ሳል በምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪወች ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቅ  በሙስናና እምነት ማጉደል ወንጀሎች እስር ቤት ገብተዋል፡፡

ነገሩን በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢወች  የሁለቱ ግለሰቦች መታሰር ፖለቲካዊ ጫና አለበት በማለት አስተያየታቸውን የፕዝዳንቱን ተግባር አጥብቀው ይተቻሉ፡፡

ሳል ምርጫውን አስመልክተው በደጋፊዎቻው ፊት ንግግር ሲያደርጉ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ፣ የቀድሞው የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አላሳኒ ኦታራ እንዲሁም የጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮ በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *