loading
ካፍ ካሜሮንን የ2019 አፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ አቅም የለሽም በማለት ነጥቋታል
አርትስ ስፖርት 22/03/2011
የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት የበላይ አካል (ካፍ) ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታስተናግድ በ2014 ነበር ዕድሉን የሰጣት፤ በየጊዜው ዘግጅቷ በሚፈለገው ልክ አልሆነም እየተባለች ስትተችም ነበር፤ ሀገሪቱ ግን እመኑኝ አላሳፍራችሁም ስትል በአደባባይ ስትናገር ቆይታለች፡፡
ካፍ ውሳኔውን ያሳለፈው ባለስልጣናቱ ትናንት በጋና መዲና አክራ ተገናኝተው ከአስር ሰዓታት በላይ የፈጀ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ነው፡፡ ካፍ እንዳለው ካሜሮን አዘጋጅነቱን የተነጠቀችው ከስድስት ወራት በኋላ በሰኔ ወር ለሚካሄደው ውድድር መሰናዶሽ ብቁ አይደለም በማለት ነው፡፡
የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የጎርጎረሳውያኑ ዓመት 2018 ከመጠናቀቁ በፊት የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር እናስታውቃለን ብለዋል፡፡
ቢቢሲ ስፖርት በዘገባው እንዳሰፈረው ግን ውድድሩን ሞሮኮ የማስተናገድ ዕድል እንዳላት የጠቆመ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ እና ግብፅም ተተኪ ሀገራት  ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡
ካፍ እንዳስታወቀው ከሆነ ካሜሮን ወደፉት ለሚደረግ ውድድር ሁነኛ ተመራጭ ሀገር ልትሆን እንደምትችል ነው፡፡ ነገር ግን የአሁኑን አዘጋጅ ሀገር ጉዳይ በጥልቀት እያጤነው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *