loading
በአዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከትራፊክ ፍሰት ነፃ የሆነ ቀን ለማክበር ሚዘጉት መንገዶች ይፋ ሆኑ

አርትስ 20/03/2011

ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ ሁለት መንገዶች የተለዩ ሲሆን አንደኛው ከጊዮርጊስ አደባባይ- በቸርችል ጎዳና-ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጊዮርጊስ አደባባይ -በ6ኪሎ-በ5ኪሎ አድርጎ መድረሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ዘ/መንፈስ ቅዱስ ፤የስኳር፣የደም ግፊት እና የጡት ካንሰር ነጻ የምርመራ አገልግሎትም ይሰጣል ብለዋል፡፡

በእለቱ የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የጤና መልእክቶች ይተላለፋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ባለሙያ አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በበኩላቸው በእለቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ የአካል ብቃት ባለሙያዎችም እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የፊታችን  ህዳር 30 በሚካሄደው ከትራፊክ ፍሰት ነጻ ቀን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ሲሆን ፤በዕለቱ ከ3ሺ እስከ 5ሺ ሰዎች ይሳተፋሉ  ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሮግራሙም ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት የሚካሄድ መሆኑንም ታውቋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *